ዦጋ
ዦጋ ከስማዳ ወረዳ ዋና ከተማ ከወገዳ ከ85 ኪ.ሜ በኋላ በየኳሳ ቀጠና ቀበሌ 33 የሚገኝ መስህብነት ያለው የተፈጥሮ ቅርስ ነው፡፡ ዦጋ የበሽሎ ወንዝ ከወደ ደሴ የአባይ ወንዝ ከወደ ባህርዳር ሁለቱ ታላላቅ ወንዞች የሚገኝበት ከመሆኑ በተጨማሪ ደ/ወሎ ጐንደር እና ምስ/ጐጃም ዞኖች 3/ሶሰት ጐልቻ የሚሰሩበት በተፈጥሮ መስህብነት ያለው ዝቅተኛ ቦታ የዦጋ ዋና ዋና ጠቀሜታ በተፈጥሮው ካሉ የውሃ የመሬት ጸጋ አንጻር ለኢንቨስትመንት ምቹ መሆኑ፣ 2. ሁለቱን ወንዞች /አባይና በሽሎ/ በግራ በቀኝ በመጠቀም የተንጣለለው የዦጋን ለም መሬት በመስኖ ማልማት እየተቻለ መሆኑ፣ 3. አትክልትና ፍራፍሬ የቅባት እህሎች/ቦለቄ፣ ሰሊጥ፣በርበሬ፣ ሌሎች የገበያ ምርቶች ማልማት፣ 4. የእንሰሳት እርባታ የቀንድ ከብቶች፣ የጋማ ከብት፣ ፍየል፣የአሳ ሀብት ልማት፣ ንብ ማነብ፣ 5. የጀልባ ትራንስፖርት፣ አገልግሎት በሁለቱ ወንዞች ማስፋፋት/የማእድን ኢነርጅ ማፈላለግ ተዝቆ የማያልቀውን የበሽሎን አሸዋ መጠቀም፣ 6. የሀይድሮ ኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫ መጠቀም፣ 7. ለሀገር ውስጥና ለውጭ ሀገር የቱሪዝም መዳረሻ ልማት በማድረግ ህ/ሰቡንና መንግስትን በኢኮኖሚው ዘርፍ/ከቱሪዝም ገቢ ማስገኘት፣ በስማዳ ወረዳ በወረዳው ግ/ል/ጽ/ቤት አዳራሽ የወረዳው ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ከ227አድባራት ኃላፊዎች ጋር ህዳር 30/03/ 2007 ዓ/ም ስለ ቅርስ መዝገባ ቁጥጥርና ጥበቃ ውይይት ሲካሄድ በቦታው በመገኘት ለመዝገብ ተችሏል፡፡ የጽ/ቤቱ የቅርስ ምዝገባና ቁጥጥር ባለሙያ አቶ ደስታው ይንገስ እንደገለፁት የአብያተ ክርስቲያናትን ሀብት የሆኑ ፅላት፣ መፅሀፎችና መሰል ንብረቶች ከጠፉበት ከዘራፊዎች ሲገኙ ንብረትነታቸው የማን እንደሆኑ ለመለየት ያስቸግር እንደነበርና የቤተክርስቲያንንም ንብረት ጠባቂዎች ተጠንቅቀው እንዲጠብቁ ያልተደረገበት እንደነበር ጠቅሰው ለውይይት ተካፋዩ አብራርተዋል፡፡ ስለዚህ የዚህን ችግር ለመፍታት ያብያተ ክርስቲያናት ቅርሶች ተመዝግበው ሊያዙና ሊጠበቁ እንዲችሉ ማድረግ የሚገባንን መወያየት አለብን በማለት አሳስበዋል፡፡ በዚሁ ውይይት የስማዳ ወረዳ ቤተ-ክህነት ኃላፊ ቄስ በእውቀት መንገሻ ያብያተ ክርስቲያናት ንብረት በመመዝገብ በመረጃ መያዝ እንዳለባቸው ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ከዚህ ጋር በተመሳሳይ የቀበሌ 32 ቄስ ቄስ ሀይማኖት አክሊሉ ምዝገባው የቤተክርስቲያን ንብረቶች ተመዝግበው ሲጠፉ ለይተን መያዝ እንችላለን ብለዋል፡፡ የስማዳ ወረዳ ፓሊስ ጽ/ቤት ኢንስፔክተር አክሎግ አዲስ እንደገለፁት እንደማንኛውም ተቋማት ቤተክርስቲያናት ሲዘረፉ ፓሊስ ዝም ብሎ እንደማያይ በማስታወስ ከዚህ በፊት ተዘርፈው የተያዙ ንብረቶች ሲመረመሩ አብዛኞቹ የቄስ እጅ እንዳለበት ዘርዝረዋል፡፡ በመጨረሻም የአድባራቱ አላፊዎች የቤተ-ክርስቲያን ንብረቶች ተመዝግበው መያዝ እንዳለባቸውና መጠበቅ እንዳለባቸው በመስማማት ውይይቱ ተጠናቋል፡፡ ታሪካዊ ገዳም ደብረ እንቁ ማርያም ደብረ እንቁ ማርያም ከስማዳ ወረዳ ዋና ከተማ ወገዳ 35 ኪ.ሜ በመኪና የኳሳ ከተማ ከደረሱ በኋላ 5 ኪ.ሜ በእግር ተጉዘው በቀበሌ 35 የምትገኝ የቦታው መልክአ ምድራዊ አቀማመጥ እጹብ ድንቅ የሆነች ከወሎዋ ግሸን ማርያም ጋር ተመሳሳነት ያላት ቦታ ናት፡፡ ቦታው ዙሪያውን ገደል መሀሏ ሜዳ ከመሆኑ በተጨማሪ ከገደሉ ስር ከአለት ድንጋይ ስር ከዋሻው ከዋሻ ውስጥ የፈለቀው ጸበል ተአምር ያሰኛል፡፡ ከቦታው ለመድረስ ትንሽ ሲቀረው ቀጭን ወንዝ የተባለውን ሜዳ ጨርሶ ወደ ደብረ እንቁ ማርያም ለመሆን ዙሪያውን ገደል ሆኖ በቀጭን መንገድ ቀስ ብለው ብለው ሲሄዱ በተፈጥሮ ላይ ግምት ይወስዳሉ፡፡ ደብረ እንቁ ማርያም የተመሰረተችበት በአፄ ካሌብ ዘመነ መንግስት /485-515/ በአቡነ ፊሊጶስ እንደሆነ ይነገራል፡፡ |
በስማዳ ወረዳ የታሪካዊ ቦታ ጉብኝት ተደረገ በወረዳ ካሉ ታሪካዊ ገዳማት መካከል በቀበሌ 35 የደብረ እንቁ ማሪያም ገዳም አንዱ ሲሆን ከስወ/ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ጋር በመተባበር በክብር በአሉ በመገኘት ጉብኝት ተካሂዷል፡፡ የቀድሞ የገዳም አስተዳዳሪ የነበሩት መላከ ስብአት አረጋ ሠርፄ እንደገለጹት ገዳሟ በ33 ዓ/ም በካሌብ ዘመነ መንግስት የተተከለች መሆኗንና ለ20 አመትም በድንኳን የተቀመጠች እንደነበር ገልጸው በርካታ መነኩሳትም እንደሚኖሩባትና የድጓና የቅኔ መምህር በገዳሙ ያሉ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ገዳሙ ከየኳሳ ታዳጊ ከተማ በእግር መንገድ 1 ስዓት የሚወስድ ሲሆን ከተራራ ላይ የተሰራ ስለሆነ ወደ ገዳሙ የሚመጡ ተገልጋዩች መንገዱ ከአንድ ሰው በላይ የማያስተላልፍ ስለሆነ እየተጠባበቁ ወደ ገዳሙ ይዘልቃሉ፡፡ ታሪካዊ ገዳም ደብረ እንቁ ማርያም ደብረ እንቁ ማርያም ከስማዳ ወረዳ ዋና ከተማ ወገዳ 35 ኪ.ሜ በመኪና የኳሳ ከተማ ከደረሱ በኋላ 5 ኪ.ሜ በእግር ተጉዘው በቀበሌ 35 የምትገኝ የቦታው መልክአ ምድራዊ አቀማመጥ እጹብ ድንቅ የሆነች ከወሎዋ ግሸን ማርያም ጋር ተመሳሳነት ያላት ቦታ ናት፡፡ ቦታው ዙሪያውን ገደል መሀሏ ሜዳ ከመሆኑ በተጨማሪ ከገደሉ ስር ከአለት ድንጋይ ስር ከዋሻው ከዋሻ ውስጥ የፈለቀው ጸበል ተአምር ያሰኛል፡፡ ከቦታው ለመድረስ ትንሽ ሲቀረው ቀጭን ወንዝ የተባለውን ሜዳ ጨርሶ ወደ ደብረ እንቁ ማርያም ለመሆን ዙሪያውን ገደል ሆኖ በቀጭን መንገድ ቀስ ብለው ብለው ሲሄዱ በተፈጥሮ ላይ ግምት ይወስዳሉ፡፡ ደብረ እንቁ ማርያም የተመሰረተችበት በአፄ ካሌብ ዘመነ መንግስት /485-515/ በአቡነ ፊሊጶስ እንደሆነ ይነገራል፡፡ ጅብና አህያ ፍል ውሃ ፀበል በአማራ ክልል በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን በስማዳ ወረዳ ከወገዳ ከተማ በደቡብ ምስራቅ አቅጣጫ በግምት 25 ኪ.ሜ ተጉዘን በጥንታዊዋ ሀገረ ቢዘን መቅደሰ ማሪያምና በቆማ ፋሲለደስ ምስራቅና ምእራብ ሁለት ተፎካካሪ እረዣዥም ሸንተረሮችመካከል በቅርብ ርቀት ከአባይ ወንዝ ጋር ከሚቀላቀለው የይባ ጅረት ስምጥ ዳርቻዎች ውስጥ የሚፈሱ የጅብና አህያ ፍል ውሀ ጸበሎች ከ15 በላይ የሚሆኑ በሻንዳና በምንጭ መልክ ወደ ላይ የሚፈሱ የህሙማን መፈወሻ ጸበሎች አሉት፡፡ የይባ ወንዝ የእስቴና ስማዳ ወረዳዎች መክፈያ ደንበር ሲሆን 10 የሚሆኑ ሻንዳ የሚበዛባቸው ከምስራቅ አቅጣጫ የሚፈሱ ፍል ውሀ ጸበሎች በስማዳ ወረዳ ሲገኙ በዚሁ አንጻር በተለያየ እብጠትና በደምስሮች መጣበብ ሽባ የሆኑ እጅና እግሮችን የመገጣጠሚያ አካላት ቁርጥማትና መተሳሰርን በከፍተኛ ሙቀት ሴሎችና የደም ስሮች እንዲፍታቱና የተቆለፉ መተጣጠፊያዎች እንዲዘረጉ በማድረግ ወደነበሩበት ጤናማ አካል የመመለስ ሀይል አለው፡፡ እንደመዥገር ራስና የስለታማ ቁስ ቁራጮች በቆዳ ውስጥ ተቆርጠው ቢቀሩ በሙቀት ሀይል ቆዳን በማላላትና በመለጠጥ ሾልከው እንዲወጡ ያስችላል፤ ንጹህ ውሀ መስሎ የሚፈላውና ጣእሙ ከመደበኛው ውጫዊ ምንጭ ውሀ እጅግ በጣም ስለቅርስ ምዝገባና ጥበቃ ውይይት ተካሄደ በስማዳ ወረዳ በወረዳው ግ/ል/ጽ/ቤት አዳራሽ የወረዳው ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ከ227አድባራት ኃላፊዎች ጋር ህዳር 30/03/ 2007 ዓ/ም ስለ ቅርስ መዝገባ ቁጥጥርና ጥበቃ ውይይት ሲካሄድ በቦታው በመገኘት ለመዝገብ ተችሏል፡፡ የጽ/ቤቱ የቅርስ ምዝገባና ቁጥጥር ባለሙያ አቶ ደስታው ይንገስ እንደገለፁት የአብያተ ክርስቲያናትን ሀብት የሆኑ ፅላት፣ መፅሀፎችና መሰል ንብረቶች ከጠፉበት ከዘራፊዎች ሲገኙ ንብረትነታቸው የማን እንደሆኑ ለመለየት ያስቸግር እንደነበርና የቤተክርስቲያንንም ንብረት ጠባቂዎች ተጠንቅቀው እንዲጠብቁ ያልተደረገበት እንደነበር ጠቅሰው ለውይይት ተካፋዩ አብራርተዋል፡፡ ስለዚህ የዚህን ችግር ለመፍታት ያብያተ ክርስቲያናት ቅርሶች ተመዝግበው ሊያዙና ሊጠበቁ እንዲችሉ ማድረግ የሚገባንን መወያየት አለብን በማለት አሳስበዋል፡፡ በስማዳ ወረዳ የሚገኙ የባህላዊ ቅርሶች መስህብ ሀብቶች |