contact
Home
Sector
communication
SPORT
tourism
high school
>
Register
login
astedader
hospital
Register
login
college
Register
login
simada history
ABOUT US
feedback
GRADE 8
በስማዳ ወረዳ የሙጃ ሮቢት አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የመማርያ ክፍል ጥበትን እና የቤተ-መጽሀፍት ችግርን ለመፍታት ጥረት እያደረገ መሆኑ ተለጸ ፡፡
የሙጃ ሮቢት አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ር/መ ምህር አቶ ፍስሃ ከፍያለው እንደገለጹት የት/ቤቱን የመማርያ ክፍል እጥረት ለመቅረፍ የሰዴ ሙጃ ልማት ማህበርና በአልማ ስማዳ ቅርጫፍ ደጋፊነት ደረጃውን የጠበቀ 4 መማሪያ ክፍሎች ያሉት አንድ ብሎክ በመገንባት ላይ ነው፡፡ ግንባታው 95 ኘርሰንት የደረሰ ሲሆን ለግንባታው እስከአሁን 597 ሽህ ብር ወጭ መደረጉን ጠቁመው ከዚሁ ጋር በተያያዘ አልማ ስማዳ ቅርንጫፍ ድጋፍ ደረጃውን የጠበቀ ቤተ-መጽሀፍት 870ሽ ብር በሆነ ወጭ እየተገነባ ሲሆን ግንባታው 95ፐርሰንት የደረሰ ሙኑን ገልጸው የመጨረሻ ክፍያውን ለማጠናቀቅ እጥረት አለብን ብለዋል፡፡
የስማዳ ወረዳ መምህራን ማህበር 19ኛ መደበኛ ምክክር ጉባኤ ከ121 ት/ቤቶች የመጡ መሰረታዊ መምህራን ማህበር አመራሮችና ፤ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በምክክር ጉባኤው ተገኝተዋል፡፡
በምክክር ጉባየው የስማዳ ወረዳ መምህራን ማህበር ሊቀመንበር አቶ ጤናው ጣሴ የበጀት አመቱ የማህበሩን ስራ እንቅስቃሴ በሪፖርት ገልጸዋል፡፡
በሪፖርታቸውም የትምህርት ጥራትና ተደራሽነትን ለማሳለጥ ማህበሩ እየተወጣ ያለውን እንቅስቃሴ ከእናት መ/ቤቱ ጋር በመሆን የመምህራን መብትና ጥቅማጥቅም በማስከበር በኩል እንዲሁም ጥሩ ውጤት ለመጡ ተማሪዎች ድጋፍ በማድረግ እንቅስቃሴ ማድረጉን በሪፖርት ተወስቷል፡፡
በምክክር ጉባኤው በቀረበው ሪፖርት የሚመለከተው አካል በኩል የሚፈቱ ተብለው ከቀረቡት መካከል የክረምት የመምህራን ደመወዝ አንድ ጊዜ አለመከፈል፤ የአማራም መምህራን ደረጃ እድገት፤ ለመምህራን መኖሪያ ቤት መስሪያ አለመስጠትና በግል የሚማሩ መምህራንና ሌሎችም ሀሳቦች ቀርበዋል፡፡በምክክር ጉባኤው ተሳታፊ የሆኑት መምህራን መኮነን አቻው የመምህራን የሙያ ፈቃድ በተመለከተ ዝውውርና የድጋፍ አሰጣጥ እንዲሁም የክረምት ትምህርት በተመለከተ ጥያቄዎችን አንሰተዋል፡፡ በተጨማሪም መምህር ንጉሴ አስራደ እንደገለጹት ከገጠር ወደ ከተማ ለመምጣት የመኪና ችግር መኖር ፖሊሶች ለመምህራን የሚሰጡት አመለካከት ዝቅተኛ ነው ከሌሎች ጋር እኩል አያዩንም እና ሌሎችን ጥያቄዎች አንስተዋል፡፡
በውይይቱ በተነሱ ጥያቄዎች ላይ የሚመለከታቸው ምላሽ ተሰጥቷል፡፡ የስማዳ ወረዳ ብአደን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አበበ እምቢያለ በተነሱ ሀሳቦች ላይ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ በመጨረሻም አባላት ምላሽ በመስጠት ተጠናቋል፡፡