የ ስማዳ ወረዳ ታሪክ
የ ስማዳ ወረዳ ታሪክ
ስማዳ ወረዳ በምስራቅ ደቡብ ወሎ ዞንና ታች ጋይንት ወረዳ፣ በምዕራብ ምስራቅ እስቴ ወረዳ፣ በሰሜን ላይ ጋይንት ወረዳ እንዲሁም በደቡብ ምስራቅ ጐጃም ዞንና ደቡብ ወሎ ዞን ያዋስኗታል፡፡
የወረዳዋ ዋና ከተማ ወገዳ ከዞኑ ዋና ከተማ ደብረታቦር 1ዐ5 ኪ.ሜ እንዲሁም ከክልሉ ዋና ከተማ ባህርዳር 2ዐ5 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ትገኛለች፡፡ ወረዳዋ በ1 መሪ ማዘጋጃ ቤት፣ በ8 ንዑስ ከተሞች ፣ በአንድ የከተማ ቀበሌ እና በ39 የገጠር ቀበሌ አስተዳደሮች የተዋቀረች ስትሆን አጠቃላይ የህዝብ ብዛትም እንደሚከተለው ነው፡፡
የህዝብ ብዛት ወንድ ሴት ድምር ፐርሰንት
በገጠር 118,3ዐ3 121,215 239,518 94.29%
በከተማ 6,195 8,303 14,498 5.71%
ድምር 124,498 129,518 254,016 100%
ፐርሰንት 49.01 % 50.99% 100%
የቆዳ ስፋቷ 228.72 KM2 ሲሆን ደጋ፣ወይናደጋ እና ቆላ የአየር ፀባይ አካትታ የያዘች እንዲሁም ሜዳማ፣ ሸለቋማ ፣ ኮረብታማና ተራራማ የመሬት መልክዓምድራዊ አቀማመጥ የወረዳዋ ማራኪ ገጽታዎች ናቸው፡፡ በተጨማሪም የስማዳ ወረዳ በርካታ ሰው ሰራሽና ተፈጥሮአዊ ቅርሶች መስህብ ባለቤት ስትሆን የዚህ አጭር ሰነድ ዓላማም በወረዳዋ ውስጥ የሚገኙትን ዋና ዋና ሰው ሰራሽና የተፈጥሮአዊ ቅርሶችን ማስተዋወቅ ሲሆን የወረዳዋን አጠቃላይ ሁኔታ ለማስተዋወቅ እና ወደ ፊት ለሚደረጉ ማንኛውም ጥናቶች በመረጃነት እንደሚያገለግል በማሰብ ነው፡፡
የወረዳዋ ህዝብ አኗኗር
የወረዳዋን የህዝብ አኗኗር ስንመለከት ህዝቡ የሚኖረው /የሰፈረው በደጋ 52%፣ በወይና ደጋ 14%፣ በቆላ 4ዐ% ሲሆን በገጠር የሚኖረው አርሶ አደር እንደየ አካባቢው የአየር ፀባይ የተለያዩ ሰብሎችን በማምረት የእለት ከእለት ፍጆታቸውን በማሸነፍ ላይ ይገኛሉ፡፡ የወረዳዋ የሙቀት መጠን 18.39 ድግሪ ሴልሽየስ ይደርሳል፡፡ የመሬት አቀማመጡን ስንመለከት 55% ተራራማ 3ዐ% ሜዳ፣ 1ዐ% ወጣ ገባና 55% ሸለቋማ ስማዳ ከፍታዋ ከባህር ወለል በላይ 246ዐ ሜትር ይደርሳል፡፡ በሌላ በኩል የዝናቡ መጠን ከ1ዐዐዐ እስከ 15ዐዐ ሚ.ሜ በአማካይ እንደሚደርስ ይገመታል፡፡
ለምሳሌ ከሚያመርቷቸው ምርቶች ድሮ ከስማዳ ወደ ተለያዩ ክፍለ ሀገራት በብርቅና በድንቅነት እየተጫነ ለነገስታቶች ሳይቀር ወደ አዲስ አበባ ከየሚለካው ወረዳዋን ከሚያስጠራት ስይት ጤፍ ጀምሮ እንደ ስንዴ፣ ገብስ፣ዳጉሳ፣ዳቡጤ፣ቦለቄና ወ.ዘ.ተ የመሳሰሉትን በማምረት በተጨማሪም በአትክልትና ፍራፍሬ በኩል ደግሞ አርሶ አደሩ ሌት ተቀን ውርጭና ሀሩር ሳይበግረው ከ1ዐ ኪ.ሜ ያላነሰ በመጓዝ ውሃ በመቅዳት እንደ ሙዝ፣ ፖፖያ፣ ሎሚ፣ ቲማቲም፣ ሽንኩርተ፣ ቃሪያ፣ በማምረት የሚተዳደር ነው፡፡ በአጠቃላይ ወረዳዋ ለኢንቨስትመንት ምቹ የሆነ የመሬት አቀማመጥና መልካም መስተዳደርና ያላት ነች፡፡
የስማዳ ወረዳ ስም አሰያየም
አሁን የምንገልጸው ስለ ወረዳችን የመጠሪያ ስሞች አሰያየም አፈ ታሪካዊ ትንታኔ ይሆናል፡፡
አፈ ታሪክ 1 የስማዳ መጠሪያ ስለሆነው “ስማዳ”
ስማዳ የሚለውን ስያሜ ያገኘችው ዓመተ ምህረቱ በውል ባይታወቅም ቀድሞ ከነበረው የከተማ መነሻዋ ከሆነው “ቀንበር በር” ከሚባለው ቦታ ነበር” ቀንበር በር የድሮው የበጌምድር ከተማ ነበረች፡፡ ከፍተኛ/አውራጃዋ/ ጋይንት ነበር፡፡ በዚህ አውራጃ እየተዳዳረች ሳለ የህግ ታራሚም የሚጐበኘው /የፍርድ ሂደት/ የማካሄደው ከአውራጃው በሚመጡ የ6 ወር ቆይታ ምርመራ ነበር፡፡ ወንጀለኞች ወደ ቀንበር በር የሚመጡትም በቀጠና ክፍል በሚመሩ በቀኝ አዝማች በግራ አዝማች፣ በፈረሰኛ፣ በጭሰኛ፣ ወ.ዘ.ተ አለቆች ነበር፡፡ በእነዚህ የተገደዱ ወንጀለኞች በቀጥታ ወደ ቀንበር በር ይመጣሉ፡፡ በበረትም ይዘጋሉ 6ወር ሲሆን ከአውራጃ በመጣ ባለስልጣን እንደተገኙበት አቀማመጥ ቃለ መጠየቅ ይደረጋል ፡፡የቃለ መጠይቁም ጀማሬ ወንጀለኛውን ምን አድርገህ ነው የመጣህ የሚል ጥያቄ ብቻ ነበር ከዚያ እንደየ ወንጀሉ ክብደት ይገረፋል፡፡ካስፈለገም እስር ይጨመርለታል፡፡
በአንድ ወቅት በሴት ማባለግ የታሰረ እስረኛ ይጠየቃል፡፡ ነገሩ እንዲህ ነበር ሰውየው መንገድ እየሄደ ሳለ ስንቁ አልቆበት መንደር ለልመና ጐራ አለ፡፡ ስዓቱ ጊዜ ነበር የራበኛ መንገደኛ ብሎ ቃሉን ከአንድ ቤት በራፍ ቆመ በዚያ ቤት ያለችው እመቤትም ግባ ብላ እህል ውሃ ስጥታው ሳለ እሱም የብሶቱን ከእህል ውሃው ጋር ይታገል ነበር፡፡ በድንገት አይኗ ይቀላውጥ የነበረችው እመቤት የእንግዳው መልክ መልካምነት ውልብ ማለት ከጀመረ ደቂቃዎች አልፈዋል፡፡ አሁንም እሱ ወደ እሷ መልክ/እይታ ለመዞር/ አልከጀለም ነበር፡፡ እሷ የእሱን መልክ ተመልክታ ለመታገስ አልቻለችምና አቀፈችው ሰውየው ደንግጦ ወዲያው እንደተጠመጠመችበት አንገቱን ሳመችው ፡፡ የፍቅር ለዚያውም የስማት ፍላጐት ነበር፡፡ አዎ ወንድ ልጅን አቅፎ መሳም ከምን ለምን ከሚል ሃሳብ የወሲብ ፍላጐት መሆኑ እሱስ መቼ እርሳውና---- ከዚያ በኋላ የወሲብ ጨዋታ ተጫወቱ፡፡ ከመቅጽበት ባል የተባለው የቤት አሳዳሪው ከተፍ አለ፡፡ ደረሰባቸው እሱም/አሳዳሪው በሆነው ጉዳይ ከመቅጽበት በመናደድ የዱላ ውረጅብኝ ከእንግዳው ከሚስቱ ላይ እሠፈሰሰ ሳለ እንግዳውም ህይዎቱን ለማትረፍ የሞት ባይ ተጋዳይ አቅሙን እያሳረፈ ኡኡታውን ለቀቀው፡፡ አንድ ከሰፈሩ የጭቃ ሹም ደረሱ እና ሶስቱንም ወደ ቀንበር በር ወስዶ እስር ቤት ሳይገቡ ባል እና ሚስቱን ወደ ሰፈራቸው ሲመለሱ ያ እንግዳ ወንጀለኛ እስር ቤት ገባ፡፡ በአራተኛው ቀን ላይ እያለ ከአውራጃ መንፈቃዊ መረጃ መጣ፡፡ ወንጀለኛው ከተመረመረ በኋላ የጅራፍ ግርፋት እያገኘ ገንዘብ እየከፈለ ብሎም ይህንን ያህል ማደጋ እህል ክፈል፣ ይህንን መሬትክን ስጥ፣ ብዙ አይነት ፍርድ እያኘ ሲፈረድበትና ሲለቀቅ ይህ መንገደኛ ቃሉን ሲሰጥ ምን ሰርተህ ነው ሲባል እንግዳ ነበርኩ እየበላሁና እየየጠጣሁ ሳለ፡፡
2/
ወይዘሮይቱ ሳመችኝ ከዚያ እንተኛ ተባባልን፡፡ ብሎ ቃሉን ሲሰጥ የአውራጃው መርማሪ ብይን ለመስጠት ተቸገረ”” አይ አንተ ቆይ አሁን እዳህን አትሰማም ቆይ ብለውት ሄዱ፡፡ ማታ ፍርድ ሰጭ ስለ ፍርድ አሰጣጣቸው ሲናገሩ አንድ ገና እዳውን የሚሰማ አለ እንጅ ሁሉም ወንጀለኛ ፍርዱን አግኝቷል ብለው እና በሁለተኛው / በቀጣዩ ዙር እዳውን የሚሰማውን ወንጀለኛም እሳቸው አንድ ሰው ብቻ ዛሬ ፈረድኩ ያንኑም ባለፈው ስሄድ እዳህን ትሰማለህ ብየ ነበር ያልኩት አሉ፡፡ የዚያ እስረኛ በዳግም ሲመጡ እሱን ብቻ ስላዩ እዳህን ስማ ብለው ስለነበር ስማዳ ተብሎ ሲደጋገም ስማዳ ተባለ፡፡
የወረዳው ታሪክ አመሰራረትና እነማን እንደመሰረቱት
የወረዳዋ አመሰራረት በድሮው ጊዜ እስቴ እና ስማዳ ከብጅና ወዲህ አንድ ወረዳ እንደነበረች መረጃው ይጠቁማል፡፡ ከዚያም በኋላ በ1927 ዓ.ም ሰኔ 12 ቀን ከእስቴ ተገንጥላ ራሷን ችላ ከጨፋ ወዲህ ሙጃና ሰዴን በመጨመር ራሱን ችሎ አንድ ወረዳ እንድሆን ሲወሰን በ1927 ሰኔ 12 ቀን የስማዳ ወረዳ ከተማ አፍቀራ መድሐኒያለም ሁና እንድትሰየም በዚያን ስዓትም ጠቅላይ ገዥ ደጃች አዩ ታደሰ እንዳስተዳድሯት ተወሰነ፡፡
ከዚያም በኋላ በ1928 ጥር 18 ቀን ቀንበር በር ከተማ እንድትቆረቆር ተደረገች፡፡
እንደገና ከ1942-1945 ደጅ አዝማች አዩ ተደሰ ስልጣኑን ተረክበው በቀንበር በር ከተማ 1945 ዓ.ም በትረ ስልጣኑን በመረከብ እየገዙ ሳለ 1946 ዓ.ም ቀንበር በር ከተማን በመተው ወደ አዲሷ አሁን ኮሽ የድሮው ተክሉ ከተማ ተቆረቆረ፡፡ ይህም ገዥ እስከ 1956 ዓ.ም ሲገዙ ቆዩ፡፡ ከዚያም በ1957 ዓ.ም ፊታውራሪ መስፍን አስፋው ተሾመ፡፡ በተደጋጋሚ እስከ 196ዐ ዓ.ም ሲገዙ ከቆዩ በኋላ በ1961 -1966 ዓ.ም ቀኝ አዝማች ዳምጤ መንገሻ ሲገዙ ቆዩ፡፡ በ1967 ዓ.ም ቀኝ አዝማች ከበደ ወንድይራድ ተሾሙ፡፡ ወዲያውኑ መርሻ የማነ ተሾሙ፡፡ አሁንም በዚህም ዓ.ም ደመክሶስ መንግስቱ እስከ 1969 ሲገዙ ከቆዩ በኋላ በ1969 ዓ.ም መቶ አለቃ መኮነን ለማ እስከ 197ዐ ሲገዙ ቆዩ፡፡ በ197ዐ እስከ 1972 ዓ.ም ግዛው ታየ ሲገዙ ቆዩ፡፡ ከ1972-1974 ሀምሳ አለቃ ስዩፍ ለገሰ በትረ ስልጣኑን ተረክበው እያለ በ1974 ዓ.ም ከተክሉ ከተማ /ኮሽ በመተው ወደ ወገዳ ከተማ ተቆረቆረች፡፡ ከተማዋም ከተቆረቆረች በኋላ እስከ 1979 አቶ ሰይፍ ለገሰ ሲገዙ ቆዩ፡፡ ከ1979-198ዐ ያለው ሽበሽ በመርክብ ገዙ፡፡
3/
ከ198ዐ-1982 ደጀን ተገኘ በመግዛት ላይ እያለ በ1982 ዓ.ም ጥቅምት 28 ቀን ኢህአዴግ በትረ ስልጣኑን ተረከበ፡፡
በወረዳው ውስጥ ያሉ ሐይማኖቶችና የተከታዩ ብዛት እና አመሰራረታቸው
በወረዳው ውስጥ የሐይማኖት ተከታዩች ሲኖሩ፡
1. የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሐይማኖት ተከታይ
የህዝብ ብዛቱም ወ 3145 ሴ 2478 ድ 136642 ሲሆን ክርስና ወደ ኢትዩጰያ ከገባበት ጀምሮ በስማዳ ወገዳም በየጊዜው በነበሩ ነገስታት አማካይነት ለመስራት ችሏል፡፡
2. የእስልምና እምነት ተከታይ የህዝብ ብዛት ወ 112ዐዐ ሴ 99ዐዐ ድ 22ዐዐዐ ሲሆን ከመካመድና በወደ በኩል በመጡ ሰራተኞች አማካይነት እንደሌላው የሀገሪቱ ክፍሎችም ወደ ስማዳም ሊስፋፋ ችሏል፡፡
3. የእምነት ተከታይ ወንጌላዊያን/ ኘሮቴስታንት እምነት ተከታይ ወ 200 ሴ 5ዐ ድ 250
የወረዳዋ ዋና ከተማና የንዑስ ከተሞች አሰያየም
በወረዳው ውስጥ እንደ የወገዳ ከተማና 8 ንዑስ ከተሞች ያሉት ሲሆን፡-
1. ወገዳ፡- የተባለበት ምክንያት ከተማው ከመቆርቆሩ በፊት ችግርና እዳ የበዛበት ዘመን ስለነበር እዳ ወግድ እንግዲህ በማለት ወገዳ ተብሎ ተሰየመ፡፡
2. ቀንበር በር፡- የተባለበት ምክንያት በወቅቱ የነበረው ገዥ በጣም አሰቃቂና ሌቦችን ሲይዙ በቀንበር በማር ይገረፍ ስለነበር ቀንበር በር ተብሎ ተሰየመ፡፡
3. የኳሳ ፡- በአካበቢው በሚገኘው ወንዝ በመውረድ አንድ ሰውየ አሳ ለማምጣት ወደ ወንዝ ወርዶ ሲመጣ ከአፋፍ ከዘለቀ በኋላ ትልቅ ዋርካ ስር አሳውን ይዞ ቁጭ አለ፡፡ ከዚያም ቦታ አርፎ ሲነሳ አንድን አሳ ትቶት ሄደ፡፡ በአጋጣሚ ሁለት ሽማግሌዎች ሲያልፉ ከዋርካው ስር አንዱ ሽማግሌ አሳውን አየና ያ ምንድን ነው ሲለው ያ እኮ አሳ ነው አለው ከዚህ በመነሳት የኳሳ የሚል ስያሜ ሰጠው፡፡
4. ተክሉ ከተማ፡-የድሮ ገዥዎች የባለ አባትነት ስሜት ስለሚሰማቸው የአባትን ስም ለማስጠራት በሚያደርጉት እሽቅድምድሚያ የአንደኛው ገዥ አባት ተክሉ ስለሚባል የአባቱን ስም ማስጠራት አንጻር ተክሉ ከተማ ተብሎ ተሰየመ፡፡
4/
በስማዳ ወረዳ የሚገኙ የባህላዊ ቅርሶች መስህብ ሀብቶች
2.1 ዦጋ
ዦጋ ከስማዳ ወረዳ ዋና ከተማ ከወገዳ ከ85 ኪ.ሜ በኋላ በየኳሳ ቀጠና ቀበሌ 33 የሚገኝ መስህብነት ያለው የተፈጥሮ ቅርስ ነው፡፡ ዦጋ የበሽሎ ወንዝ ከወደ ደሴ የአባይ ወንዝ ከወደ ባህርዳር ሁለቱ ታላላቅ ወንዞች የሚገኝበት ከመሆኑ በተጨማሪ ደ/ወሎ ጐንደር እና ምስ/ጐጃም ዞኖች 3/ሶሰት ጐልቻ የሚሰሩበት በተፈጥሮ መስህብነት ያለው ዝቅተኛ ቦታ LOE LAND AREA/ ነው፡፡
የዦጋ ዋና ዋና ጠቀሜታ
1. በተፈጥሮው ካሉ የውሃ የመሬት ጸጋ አንጻር ለኢንቨስትመንት ምቹ መሆኑ፣
2. ሁለቱን ወንዞች /አባይና በሽሎ/ በግራ በቀኝ በመጠቀም የተንጣለለው የዦጋን ለም መሬት በመስኖ ማልማት እየተቻለ መሆኑ፣
3. አትክልትና ፍራፍሬ የቅባት እህሎች/ቦለቄ፣ ሰሊጥ፣በርበሬ፣ ሌሎች የገበያ ምርቶች ማልማት፣
4. የእንሰሳት እርባታ የቀንድ ከብቶች፣ የጋማ ከብት፣ ፍየል፣የአሳ ሀብት ልማት፣ ንብ ማነብ፣
5. የጀልባ ትራንስፖርት፣ አገልግሎት በሁለቱ ወንዞች ማስፋፋት/የማእድን ኢነርጅ ማፈላለግ ተዝቆ የማያልቀውን የበሽሎን አሸዋ መጠቀም፣
6. የሀይድሮ ኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫ መጠቀም፣
7. ለሀገር ውስጥና ለውጭ ሀገር የቱሪዝም መዳረሻ ልማት በማድረግ ህ/ሰቡንና መንግስትን በኢኮኖሚው ዘርፍ/ከቱሪዝም ገቢ ማስገኘት፣
በአጠቃላይ ካለው ኢኮኖሚው ማለትም የግብርና መሪ ኢንዱስትሪ ፖሊሲዎችን አንጻር የሀገሪቱን የክልሉን፣ የዞኑን2 የወረዳውንና የቀበሌዎችን ልማት ለማፋጠን የሚችል በጥናት ያልታወቀ አልፎ አልፎ ግን ፈረንጆች ሳይቀሩ በሊኮፍተር፣ በጀልባ፣ ከወደ ደሴና ባህርዳር እየመጡ እያጠኑት ወይም እየጐበኙት ያለ ቦታ በመሆኑ በአጠቃላይ የግብርና ምርትን ወደ ገበያ ከማቅረብና ቱሪዝም ከማስፋፋት አንጻር ከስማዳ ደ/ጐንደር ወደ አማራ ሳይንት/ወሎ የሚጠናው መንገድ እውን ቢሆን በዦጋ የሚያስገኘው ጥቅም መጠነ ሰፊ ነው፡፡
የጅብና አህያ ፍል ውሃ ፀበል
ጅብና አህያ ፍል ውሃ ፀበል ከስማዳ ወረዳ ዋና ከተማ ወገዳ 2ዐ ኪ.ሜ በመኪና 1ዐ ኪ.ሜ በእግር በድምሩ 3ዐ ኪ.ሜ በኋላ በቀበሌ ዐ2 የሚገኝ ከደራው ዋንዛየ ጋር ተመሳሳይነት ያለው በቁስል ፈዋሽነቱ የታወቀ ፍል ውሃ ነው፡፡ በአካባቢው አጠራር መዋት ይባላል፡፡ ይህ ፍል ውሃው የሚገኝበት ወንዝ ዋሻ ይባላል፡፡ ወደ እስቴው ቆማ ፋሲለ ደስ መሸጋገሪያ ቦታ ነው፡፡ 5/
ወደ ዚህ ፀበል ለመጓዝ መንገዱ ገደላማ አስቸጋሪና ጠባብ በመሆኑ በርካታ መንገደኞች በአንድ ጊዜ ማስተላለፍ አይችልም፡፡
በዚህም የተነሳ በአንድ አህያና ጅብ በጉዞ ላይ እንዳሉ በዚህ ጠባብ መንገድ ላይ ፊት ለፊት ይገናኛሉ፡፡ አህያውም ቀድሞ የጅብን ማጅራት ነክሶ በመያዝ ጅቡ ሞቶ አህያው ነክሶ የተገኘበት ቦታ በመሆኑ የፍል ውሃውም ስም ጅብና አህያ እየተባለ እንደሚጠራ ይነገራል፡፡
በዚህ የፍል ውሃ ፀበል እስከ ስምንት /የደረሱ የተለያዩ ፀበሎች ይገኛሉ፡፡ እነዚህም 1ኛ ፋሪስ፣2ኛ አቦ፣3ኛ ቅዱስ ሚካኤል፣ 4ኛ መድሐኒዓለም፣ 5ኛ ቅዱስ ጊወርጊስ፣ 6ኛ ተክለ ሐይማኖት፣ 7ኛ ኪዳነ ምህረት 8ኛ ቅድስት ማርያም ሲሆኑ በተጨማሪም በእነዚህ አካባቢ በግምት ከ8-1ዐ ኪ.ሜ ላይ ዋክላና የሻሂ የተባሉ የፍል ውሃ ፀበሎች ይገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በቀበሌ 38 ብጅና ከተባለው ወንዝ ዳርቻ ላይ ሰርዴት የተባለ ፍል ውሃ ፀበል ይገኛል፡፡ በፈዋሽነቱ ከጅብና አህያ ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ እነዚህ ፍል ውሃዎች እንክብካቤና ጥበቃ ቢደረግላቸው መንገድ ቢሰራላቸው ከዘመናዊ ህክምና በተጨማሪ የሚሰጡት የባህል ህክምና ቀላል ግምት የሚሰጠው አይደለም፡፡
2.3 የስማዳ ፈሳሱ ላሊ በላ
ከወረዳው ርዕሰ ከተማ ወገዳ በትሰ ስሜን ምዕራብ 2ዐ ኪ.ሜ ርቀት ላይ ምክሬ ቀጠና ቀበሌ 16 ከፈሳስ ወንዝ አጠገብ ላሊ በላ እየተባለ የሚጠራ ከአለት ድንጋይ ፍልፍል ምሰሶ ግድግዳና ጣራ ከአንድ ወጥ ቋጥኝ የተሰራ ጅምር ህንጻ ይገኛል፡፡
የዚህ ህንጻ አፈ ታሪክ ንጉስ ላሊ በላ ውስጥ ሲኖር ራሱን በተመቀኙ ስዎች በተንኮል በደረሰበት በደል ይህን ሀገር አያሳየኝ ብሎ ጐጃምን ለቆ ወደ ስማዳ በመምጣት ይህን ህንጻ ስራ ጀምሮ በመስራት ላይ እንዳለ በሚሰሩበት አካባቢ ምን አይነት ሰው መጣብን በሚል ምቀኝነት ተነሳስተው ምግብ ለምታዘጋጅላቸው እርዳቸው ወይም ሰራተኛቸው የጃርት ስጋ ሰርታ እንድታበላቸው በመደረጉ እና ምግቡን በሚመገቡበት ጊዜ ጣዕሙ/ቃናው ከተለመደው የምግብ ጣዕም ለየት ስለ አለባቸው ምን አይነት ምግብ ነው የሰጠሽኝ ንገሪኝ ብለው በጠየቋት ጊዜ እነ እገሌ የጃርት ስጋ ስጭው ስለ አሉኝ ነው፡፡ ያዘጋጀሁት ብላ በነገረቻቸው ጊዜ ተቆጥተው ረዳታቸውን ከገረፏት በኋላ በአካባዉ የሚገኝ ታላቅ የወይራ ዛፍ ላይ ወጥተው ለፈጣሪያቸው ጸሎት እያደረሱ ሳለ አሻግረው ሲመለከቱ የጐጃምን መሬት በማየታቸው ለካስ አሁንም ከጐጃም በጣም ርቄ አልሄድኩም ብለው የህንጻውን ስራ አቋርጠው እንደሄዱ የነገራል፡፡ የህንጻው አሰራር ከስሜን ወሎው ላስታ ወረዳ ውስጥ ከሚገኘው የንጉስ ላሊ በላ ቤት መቅደሶች ጋር በቅርጽ ተመሳሳይ ነው፡፡
ይህ ጅምር በጥንታዊ ቅርስነቱ ለወደፊት ትውልድ በቅርስነት ጠብቆ ለማቆየት እና ለጥናትና ምርምር ምንጭ እንዲሆን አስፈላጊውን እንክብካቤና ጥበቃ እንዲደረግለት ይሻል፡፡
2.4 አንፋርጌ ጊወርጊስ
አንፋርጌ ጊወርጊስ ከስማዳ ወረዳ ዋና ከተማ ወገዳ ከተማ 8ዐ ኪ.ሜ ወደ ሙጃ ሮቢት ከተማ ለመድረስ 3 ኪ.ሜ አቋርጠው በቀበሌ 26 የሚገኝ ታሪኩና የአሰራር ጥበቡ እፁብ ድንቅ የሆነ ታሪካዊ ሰው ሰራሽ ቅርስ ነው፡፡ አንፋርጌ የሚለው ስያሜ አንፋር ከሚለው የዛፍ ስም ጋር ተያይዞ የመጣ ነው፡፡
አንፋርጌ ጊወርጊስ የተሰራው በ1335 ዓ.ም በአፄ ሰይፋርድ ዘመነ መንግስት ሲሆን የቤተ መቅደስ አገልግሎት ይሰጥበት እንደነበር ይነገራል፡፡ የአሰራር ጥበቡ ጥንታዊ ጥርብራቢ፣ ቀይ የሸክላ በኖራ፣ የተሰራ ነው፡፡ በዘመነ ብዛት በፀሐይና በዝናብ ጉዳት ደርሶበት ቆመው የሚታዩት ምሰሶዎች በዘመኑ ምን አይነት የስነ-ህንጻ ጥበበ እንደነበር ይመሰከራሉ፡፡
ዛሬ ከበፊቱ ቦታ አጠገብ በአዲስ ተሰርቶ በሚገኘው የአንፋርጌ ጊወርጊስ ቤተ ክረስቲያን ውስጥ የአንድ ጥንታዊ ሰው የአጽም ቅጅረት ይገኛል፡፡ ይህም ስለ ሰው ልጅ ታሪካዊ አመጣጥ ጥናትና ምርምር ለሚያደርጉ የአርኬዩሎጅ ሳይንሳዊ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡
አንፋርጌ ጊወርጊስ በጣሊያን ወረራ ጊዜ የወርቅ መስቀል፣ የወርቅ ሄል፣ የወርቅ ጽዋ፣ የመሳሰሉት ተንቀሳቃሽ ቅርሶች ዝርፊያ እንደተካሄደበት የደብሩ አገልጋይ ካህናት ይናገራሉ፡፡
2.5 የበለስ ግንብ
የበለስ ግንብ ከስማዳ ወረዳ ዋና ከተማ ወገዳ በስተደቡብ ምዕራብ ከ5 ኪ.ሜ በኋላ በቀበሌ ዐ3 የሚገኝ ታሪኩና የአሰራር ጥበቡ ከጐንደር የአፄ ፋሲል ቤተ መንግስት ግንብ ጋር ተመሳሳይነት ያለው የቤተ መንግስት ፍርስራሽ ነው፡፡
ይህ ሰው ሰራሽና ግዙፍነት ያለው ቅርስ በእድሜ ብዛትና እንክብካቤ ጉድለት የመፍረስ፣ የመሰንጠቅ፣ ጉዳት የደረሰበት ከግንዛቤ ማነስ የአካባቢው ማህ/ሰብ እንሰሳ ስለሚታከኩት በመፍረስ ላይ ይገኛል፡፡
የበለስ ግንብ የተሰራው መቼ? በማን? ለሚለው ጥያቄ የታሪክ ማጣቀሻ ማግኘት ባይቻልም የአካባቢው የቀድሞ አባቶች በአፈ ታሪክ እንዳቆዩት በአፄ ፋሲል ዘመነ መንግስት/17ኛው ክፍለ ዘመን ቢትወደድ መልካአ ክርስቶስ የተባለ ግለሰብ እንደሰራው ይነገራል፡፡ የቢትወደድ ወንድም ደጃይ ደመክሶስ በወቅቱ ከነበረው ንጉስ ሳያስፈቅድ በራሱ ጊዜ ግንባታውን በመስራቱ ጐንደር ድረስ በመሄድ ለአፄ ፋሲል በወንድሙ ላይ ክስ መስርቶ እንዳሳሰረው እና ቢትወደድም በእስር ቤት እንዳለ እንደሞተ የአካባቢው ተወላጆች ይናገራሉ፡፡
ይህ ቅርስ እንክብካቤና ጥበቃ ቢደረግለትም የቀድሞ አባቶቻችን ምን ያህል በእደ ጥበብ የተካሰ እንደነበር ለተተኪው ትውልድ ማስተላለፍ ከማስቻሉም በላየ ከቱሪዝም የሚገኘውን ገቢ ሊያሰድግ ይችለል፡፡
7/
2.6 ደብረ እንቁ ማርያም
ደብረ እንቁ ማርየም ከስማዳ ወዳ ዋና ከተማ ወገዳ 35 ኪ.ሜ በመኪና የኳሳ ከተማ ከደረሱ በኋላ 5 ኪ.ሜ በእግር ተጉዘው በቀበሌ 35 የምትገኝ የቦታው መልከአምድራዊ አቀማመጥ እፁብ ድንቅ የሆነች ከወሎው ግሸን ማርያም ጋር ተመሳሳይነት ያላት ቦታ ናት፡፡ ቦታው ዙሪያውን ገደል መሀሉ ሜዳ ከመሆኑ በተጨማሪ ከገደሉ ስር ከአለት ድንጋይ ስር ከዋሻ ውስጥ የፈለቀው ፀበል ታአምር ያሰኛል፡፡ ከቦታው ለመድረስ ትንሽ ሲቀረው ቀጭን ወንዝ የተባለውን ሜዳ ጨርሶ ወደ ደብር እንቁ ማርያም ለመሄድ ዙሪያውን ገደል ሁኖ በቀጭን መንገድ ቀስ በቀስ ብለው ሲሄድ በተፈጥሮ ላይ ግምት ይጀምራሉ፡፡
ደብረ እንቁ ማርያም የተመሰረተችው በአፄ ካሊብ ዘመነ መንግስት/485-515 /በአቡነ ፊሊጰስ እንደሆነ ይነገራል፡፡
2.7 የጋት ሚካኤል
የጋት ሚካኤል ቤተክርስቲያኑ ከስማዳ ወረዳ ዋና ከተማ ወገዳ በስተምስራቅ ከ2ዐ ኪ.ሜ በኋላ በቀበሌ 11 የሚገኝ በታሪኩና ሐይማኖታዊ ይዘቱ በደንጋይ ቆብ መቁጠሪያ የተለየ ገጽታ ያለው ቅርስ ነው፡፡ ይህ ቤተክርስቲያን የገነቡት አባ ጋተው መነኩሴ ሲሆኑ በአፄ ይኮኑ አምላክ /1253-1268/ ዘመነ መንግስት ነው፡፡
በአፈ- ታሪክ እንደሚነገረው መነኩሴው ብቻቸውን ቤተክርስቲያኑ ሲሰሩት ከመንፈቀ ቅዱስ ሀይል መሪነት በጣም ትልቅ የድንጋይ ቆብ ደፍተው፣ የድንጋይ ክታብ አጥልቀውና የድንጋይ መቁጠሪያ ይዘው እንደነበርና እነዚህ ነገሮችም ከትውልድ ትውልድ ተላልፈው በቤተክርስቲያኑ በቅርስነት ይገኛሉ፡፡
የድንጋይ ቆቡ 5ዐ ኪ.ግ የሚመዝን መካከለኛ ገበታ የሚያክል ሲሆን ከአለት ድንጋይ ተጠርቦ የተሰራ ነው፡፡ የራስ ማስገቢያው ሰፋ ብሎ ጐድጐድ ያለ ሲሆን ከቆቡ መጠን መተለቅ የተነሳ የመነኩሴው ራስ ትልቅ እንደነበር ያስታውሳል፡፡ ከአንገታቸው ላይ የሚያደርጉት 25 ኪ.ግ የሚመዝን የድንጋይ ክታብም ቅርጹ የቡና መውቀጫ፣ ሲመስል 3 ክርክራት ተቀርጾበታል፡፡ የድንጋይ ክታቡም መነኩሴው እንደ ሀብል አጥልቀውት አኖር ነበር ይባላል፡፡ የድንጋይ መቁጠሪያው ግን በግራኝ መሀመድ ወራሪ ጊዜ ከየጋት ሚካኤል ወደ ጐጃም ድማ ጊወርጊስ እንደተወሰደ የአካባቢው የሀገር ሽማግሌዎች ይናገራሉ፡፡
ታቦቱን የተከሉት መነኩሴ ከስራቸው በኋላ በቀን ሰባት ሽህ ይሰግዱ እንደነበርና ምግባቸውም ባቄላ በቻ ሲሆን በቀን አንድ ማድጋ ወይንም ሰባት ቁና ይመገቡ ነበር ይባላል፡፡
በዘመናት መለኪያ አንድ ቁና ቢያንስ 5 ኪ.ሜ ሲገመት ሰባት ቁና የሚመገቡት መነኩሴ 35 ኪ.ግ ድረስ ይመገቡ ነበር ማለት ነው፡፡ 8/
2.8 እንኑም አቦ ገዳም
ከስማዳ ወረዳ ዋና ከተማ ወረዳ ወደ ሙጃ ሮቢት 8ዐ ኪ.ሜ ከተጓዙ በኋላ ከሙጃ ሮቢት በስተደቡብ ምዕራብ የ2ዐ ደቂቃ የእግር ጉዞ በማድረግ ቀበሌ 26 የሚገኝ የአፄ ሰይፋአረድ ዘመነ መንግስት በ13ዐ5 ዓ.ም በተፈጥሮ ዋሻ ውስጥ የተሰራ ገዳም ሲሆን በውስጡም ለአርኪአሎጅ ጥናትና ምርምር የሚያገለግል የአጽም ቅሬት ይገኛል፡፡
በተጨማሪም ገዳሙን ልዩ የሚያደርገው በዋሻው ውስጥ ፈርድቱ የፈለቀው ፀበል የእብድ ዋሻ በሽታ፣ ለለከፈው ፍቱን መድሐኒት/ፈዋሽ/ መሆኑ ነው፡፣ ይህ ቅርስ የዋሻው ጣሪያም በጐርፍና ዝናብ ፈሳሽ በማስገባት በመሰነጣጠቅ ጉዳት እያደረሰበት ነው፡፡
2.9 ገዳም ስላሴ
ከስማዳ ወረዳ ዋና ከተማ ወገዳ 2ዐ ኪ.ሜ በመኪና ከተጓዙ 5 ኪ.ሜ በእግር ተጉዞ በምክሬ ቀጠና በቀበሌ 17 የሚገኝ በተፈጥሮ ደን የተሸፈነ ገዳም ነው፡፡ ገዳሙ የተመሰረተው በ1ዐ23 ዓ.ም በግርማ ስዩም ዘመነ መንግስት ነው፡፡
ገዳሙ በድሮው ዘመን የሴትና የወንድ ገዳም ተብሎ የንፋሮ ገዳም በመባል ይታዎቃል፡፡ገዳሙን ልዩ ከሚያደርጉት አባ እንቁ ስላሴ የባሉ መነኩሴ ሌሊት ያለ እረፍት ይፀልዩበት የነበረው ቀዝቃዛ ባህር የቃል ኪዳን ፀበል በሽተኞች ዛሬም እየፈወሰ መሆኑ ነው፡፡
2.1ዐ ገዳም ሚካኤል
ከስማዳ ወረዳ ዋና ከተማ ወገዳ 8ዐ ኪ.ሜ በመኪና ወደ ሙጃ ቀጠና ከተጓዙ በኋላ ከሙጃ ሮቢት 5 ኪ.ሜ በእግር ተጉዘው በቀበሌ 13 የሚገኝ በተፈጥሮ ደን የተሸፈነ መስህብነት ያለው ገዳም ነው፡፡ ይህ ገዳም የተመሰረተው በዓለም ሰገድ/አፄ ፋሲል/ ዘመነ መንግስት 1624-1659 ነው፡፡ የገዳሙን አሰራር ልዩ የሚያደርገው ከታች የእንጨት ግድግዳ ከላይ ድንጋይ ሁኖ ጥንታዊ እደ ጥበቡ አስገራሚ መሆኑ ነው፡፡ በዚህ ገዳም በአሁኑ ስዓት ወ 4 ሴ 4 በድምሩ 8 መነኩሳት ይገኙበታል፡፡
2.11 ሸውሃ ጊወርጊስ
ሸውሃ ጊወርጊስከስማዳ ወረዳ ዋና ከተማ ወገዳ ቀበሌ 37 ዋርካየ ዓርብ ገበያ ወይም 35 ኪ.ሜ የኳሳ ቀበሌ 35 በመኪና ከተጓዙ በኋላ 3ዐ ኪ.ሜ በእግር ወደ ሙጃ ቀጠና ተጉዘው በቀበሌ 3ዐ የሚገኝ በስለት አድራሽነቱ የታወቀና በተለይ ደግሞ ሚያዚያ 23 ቀን በሚከበረው የንግስ በዓሉ በርካታ ህዝብ የሚጓጓዝበት ሰው ሰራሽ ታሪካዊ ቅርስ ነው፡፡ ሸውሃ ጊወርጊስ የተመሰረተው በኢብርሐና አጽብሐ ዘመነ መንግስት በ332 ዓ.ም ነው፡፡
9/
2.12 ኮከብ አምባ/የሙሲልም መዘየር
ከስማዳ ወረዳ ዋና ከተማ ወገዳ ወደ ሙጃ ሮቢት 8ዐ ኪ.ሜ በመኪና ከሙጃ ሮቢት 29 ኪ.ሜ በእግር ወደ ቀበሌ 29 ነድሁ አደሬት ጣራ ልዩ ስሙ ኮከብ አምባ ከተባለው ቦታ የሚገኝ የሙሲልም መዘይር ነው፡፡ የዚህ ቅርስ መስራች ሰይድ እንዲሪስ ኑርየ በ19ዐ7 ዓ.ም አካባቢ የእስልምና ሐይማኖት ትምህርት ማስተማር እንደጀመሩና ጠንቋይና ደጋሚዎችን በሰፊው ይቃወሙ እንደነበርና በፀሎና በተሀሊል/በፀበል/ ብቻ ፈጣሪን ለምኖ ፈውስ ማግኘት እንደሚቻል ይመክሩ እንደነበር ይነግርላቸዋል፡፡
ሰይድ እንድሪስ ከሞቱ በኋላ በየ ዓመቱ በጥር ወር እና በግንቦት ወር ብዙ ህዝብ ከመቃብራቸው እየሄዱ ለተሳሉ ስዎች ያሰቡትን ሁሉ እንደሚያገኙ ቦታውንና መቃብሩን ለመጐብኘት ከተለያዩ ቦታዎች ጐብኝዎች እንደሚመጡ ነዋሪዎች ይናገራሉ፡፡
2. 13 ገሀነብ ዋሻ
ይህ ቅርስ የሚገኘው ከስማዳ ወረዳ ከተማ ወገዳ ከ15 ኪ.ሜ በኋላ በቀበሌ 11 ሲሆን ዋሻውን ልዩ የሚያደርገው መነሻ ቦታው እየታወቀ መድረሻው የማይታወቅ እና ለዘመናት ብዙ ቅርሶች የነበሩበት ዋሻ ነው፡፡
2.14 ወሰመር ዋሻ
ይህ የተፈጥሮ ቅርስ የሚኘው ከስማዳ ወረዳ ዋናከተማ ወገዳ ከተማ 28 ኪ.ሜ በመኪና 3 ኪ.ሜ በእግር በድምሩ 31 ኪ.ሜ በኋላ በቀበሌ 37 የሰው አጽም የሚገኝበት ዋሻ ነው፡፡
የሀይማኖት ባህላዊ በዓላት መረጃ
ሀ/ ሀይማኖታዊ በዓላት
ተ.ቁ የሀይማኖት በዓሉ በዓሉ የሚከበርበት ቀን ወረዳ በዓሉን ልዩ የሚያደርገው ነገር
1 በዓለ ልደት/ገና/ ታህሳስ 29 ስማዳ አየሱስ ክርስቶስ የተወለደበት ቀን መታሰቢያ
2 በዓለ ጥምቀት ጥር 11 ስማዳ አየሱስ ክርስቶስ የተጠመቀበት መታሰቢያ
3 በዓለ ደብረታቦር ነሐሴ 13 ስማዳ አየሱስ ክርስቶስ ስነ-መለኮቱን በደብረታቦር የገለጸበት መታሰቢያ
4 በዓለ ሆሰና ከትንሳኤ በፊት ያለው ስማዳ አየሱስ ክርስቶስ ወደ እየሩሳሌም ቤተ መቅደስ የገባበት መታሰቢያ
5 በዓለ ስቅለት ከትንሳኤ በፊት ስማዳ አየሱስ ክርስቶስ በመስቀል የተሰቀለበት እለት መታሰቢያ
6 በዓለ ትንሳኤ/ፋሲካ/ በየዓመቱ የሚለዋወጥ ሁኖ በእለት እሁድ ስማዳ አየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ የተነሳበት እለት መታሰቢያ
7 በዓለ ጰራቅሊጦስ ከትንሳኤ ከ5ዐ በኋላ ከእርገት ከ1ዐ ቀን በኋላ ስማዳ አየሱስ ክርስቶስ ሞቶ ከተነሳ ከ5ዐ ቀን በኋላ በእየሩሳሌም ከተሰበሰቡ ስዎች እና ሀዋርያት መንፈሰ ቅዱስ የወረደበት ቀን መታሰቢያ
8 በዓለ እርገት ከትንሳኤ ከ4ዐ ቀን በኋላ ባለው ሀሙስ እለት ስማዳ አየሱስ ክርስቶስ በፈቃዱ ሞቶ ከተነሳ ከ4ዐ ቀናት በኋላ ወደ ሰማይ ያረገበት ቀን መታሰቢያ
9 ደብረ ዘይት የአብይ ጾም መካከለኛ እሁድ ስማዳ አየሱስ ክርስቶስ ስለ ዳግም ምጻቱ ያስተማረበት ቀን መታሰቢያ
10 መስቀል መስከረም 17 ስማዳ አየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት መስቀል ከ3ዐዐ ዓመታት በኋላ ተቆፍሮ/በንግስት እሌኒ የተገኘበት ቀን/
11 ኢድ አልፈጥር ፡ የእስልምና ሐይማኖት /ጾም መፍታት/
12 ኢድ አል አድሃ አረፋ
13 መውሊድ የነብዩ ሙሀመድ የልደት ቀን
14 ፍስለታ ፋሲካ
15.የእመቤታችን ትንሳኤና እርገት በመሆኑ ንሐሴ 16
የባህላዊና ተፈጥሮአዊ ቅርሳች መስህብ ሀብቶች ጥናት የከተሞች ኘሮፋይል
በስማዳ ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት
2ዐዐ7 ዓ.ም