ትኩረት ለጤናችን
የኢቦላ በሽታ በርካታ ዜጐችን እየቀጠፈ የሚገኝ አሳሳቢ በሽታ ነው፤ይህን በሽታ ለመግተት የአለም ሃገራት በመረባረብ ላይ ይገኛሉ፡፡ ሃገራችንም ለጉደዩ ትኩረት በመስጠት እየተቀሳቀሰ ች ነው፡፡ ስለሆነም ህብረተሰቡ ስለበሽታው በቂ ግንዛቤ እንዲኖርው ይፈልጋል ሌባ እንዳይገባ በርህን ዝጋ ነውና ስለበሽታው አስከፊነት በውል ተረድቶ መከላከል ያስፈልጋል 1.የኢቦላ በሽታ ምንድ ነው፣-ኢቦላ የስሙ መጠሪያ በምዕራብ አፍሪካ ዲሞክራቲክ ኮንጐ ሪ ፓብሊክ ከሚገኝ የወንዝ ስም የተወሰደ የበሽታ ስም ነው፡፡ የኢቦላ በሽታ በቫይረስ ምክንያ ት የሚመጣ በፍጥነት ከሰው ወደሰው የሚተላለፍና በአጭር ጊዜ ውስጥ ለሞት የሚዳርግ በ ሽታ ነው፡፡ የኢቦላ በሽታ በምዕራብ አፍሪካ ሃገሮች በተደጋጋሚ በመከሰት ከፍተኛ ህመምና ሞት እያደረሰ የሚገኝ በሽታ ነው፡፡ 2. የኢቦላ በሽታ መተላለፊያ መንገዶች፡- በኢቦላ ከታመመ ሰው ቁስል ፣ደም ፣ምራቅ፣ትውከ ት ፣አይነምድርና ሽንት ጋር በቀጥታ በመነካካት ወይም እነዚህ ፈሳሾች ወደ ጤነኛው ሰው አይን ከተረጩና ከገቡ ፣ንጽህናቸው ባልተረጋገጠ ወይም ሌሎች ህሙማን የተጠቀሙበትን መርፌ ሳይቀቅሉ በመጠቀም ፣የኢቦላ በሽታ ታማሚ የተጠቀማባቸውን ስለታማ መሳሪያዎች በመጠቀም ፣ በኢቦላ በሽታ የሞተ ሰውን አስከሬን በቀጥታ በመነካካት እና በኢቦላ በሽታ የሞ ተውን እንስሳ ስጋ በመመገብ ናቸው 3. በኢቦላ በሽታ የተያዘ ሰው የበሽታውን ምልክቶች የሚያሳየው መቸ ነው በኢቦላ በሽታ ከ ተጠቃ ሰው ጋር ንክኪ የፈጠረ ሰው ከ2 እስከ 21 ቀናት ባለው ጊዜ ውስጥ የበሽታውን ምልክቶች ማሳየት ይጀምራል፡፡ 4. በኢቦላ በሽታ የተያዘ ሰው የሚያሳያቸው ምልክቶችና ስሜቶች፡- ድንገተኛ ከፍተኛ የሆነ ትኩሳት፣ማስመለስ /ማስታወክ፣ ተቅማጥና ፣ራስ ምታት ፣የቆዳ ሽፋታ እና የአይን መቅላት ምልክቶች ይታዩበታል ፤በሰውነታችን ከፍት ቦታዎች ማለትም አይን ፣አፍንጫ ፣ድድ ፣ጀሮ፣ ፈንጢጣና በብልት በኩል የመድማት ምልክት ሊታይም ላይታይም ይችላል፡፡ 5. በኢቦላ በሽታ መያዝ የተጠረጠረ ወይም የተያዘ ሰው ከገጠመን ምን ማድረግ አለብን፡- ታማሚውን በምንረዳበበት ጊዜ ሰውነታችንን ከበሽታው መከላከል የሚያስችለንን የእጅ ጓንት የአይን መከላከያ መሳሪያ /ጐግል/ እና የአፍንጫና የአፍ መሸፈኛ ማስክ መጠቀም ፤የታመመውን ሰው ወዲያውኑ ለአስፈላጊ ህክምናና እርዳታ በአቅራቢያው ወደሚገኘው ጤና ተቋሙ መውሰድ ጽ/ቤት ሪፖርት ማድረግ ፣ በሽታው መያዙ የተጠረጠረ ወይም የታመመ ሰው የተጠቀማባቸውን አልባሳትና መኝታውን በበረኪና ማጠብ ይኖርብናል፡፡ በስማዳ ወረዳ ወገዳ ከተማ ወጣቶች በመደራጀት በጋቢዩን ስራ መሰማራታቸው ተገለጸ፡፡ መስማዳ ወረዳ ወገዳ ከተማ ወጣቶች በመደራገ,ጀት በጋቢዩን ስራ መሰማራታቸውን የስ/ወ/ቴክኒክና ሙያ ኢንተር ፕራይዝ ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡ የማህበሩ ሊቀመንበር የሆነው ወጣት አበበ ቢራራ እንደለጸው ዩኒቨርስቲ ተመርቆ ስራ አለመኖሩን ገልፆ በመደራጀት ከመንስት 500 ካሬ ሜትር ቦታ ተሰጥቷቸው ስልጠና እንዳገኙና በጋቢዩንስ ስራ ተሰማርተው እያመረቱ መሆኑን ገልፆ በውስጡም ለ9 ያህል ወጣቶች የስራ እድል የተፈጠረላቸው መሆኑንና የተሰራው የጋቢወንስ ምርቱ ላይ የገቢያ ትስስር ተደርጎልን እስከ 550 ጋቢዩን እያመረትን ነው ምርቱንም አስረክበን 274.000 ብር አጠቃላይ ገቢ እንደሚያገኙ አብራርቷል ፡፡ ሌሎች ወጣቶችም የመንግስት ስራ ከሚጠብቁ እንደኛ ተቀናጅተው ወደስራ ቢገቡ መልካም ነው ጊዜአቸውንም ማባከን የለባቸውም ብሏል፡፡ የስራ እድል ከተፈጠረላቸው ወጣቶች መካከል ወጣት አብራሀም ቀለቡ እንደተናገረው ከዚህ በፊት ምንም አይነት ስራ የለኝም ነበር አሁን ግን በጋቢዩንስ ስራ ተደራጅቸ በመስራቴ በቀን 20 ጋቢዩን ስንሰራ የቀን ገቢያችን 300 ብር ይሆናል እኛም ተጠቃሚ ሁነናል በማለት ሌሎች ወጣቶችም እንደኛ ቢሰሩ ተጠቃሚ ይሆናሉ ሲል ገልጸል፡፡ የስ/ወ/ቴ/ሙያ ኢንተር ፕራይዝ ጽ/ቤት የግንዛቤ ፈጠራ ባለሙያ የሆኑት አቶ አብራራው አስማማው እንደገለጹት በጽ/ቤቱ የግንዛቤ ፈጠራና በቴክኒክ ኮሌጅ የሙያ ስልጠና ከተሰጣቸው በኋላ ወደስራ መግባት ችለዋል የገቢያ ትስስርም ተደርጎላቸው ምርቱን እያመረቱ ነው በቀጣይም በምርቱ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ገልጸዋል፡፡ |
LATEST NEWS
|
Design by endris essa