"ኢህአዴግ ለህዝብ እየሰራ ያለ ድርጅት ነው"
ኢህአዴግ ለህዝብ ተጠቃሚነት እየሰራ ያለ ድርጅት መሆኑን በተመለከትናቸው የልማት ስራዎች ማረጋገጥ ችለናል ሲሉ ሰሞኑን በቻይና አፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሴሚናር ተሳታፊ የነበሩ የአፍሪካ ገዥ ፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች አስታወቁ፡፡ ለሶስት ቀናት ሲካሄድ በነበረው ሴሚናር ላይ ተሳታፊ የነበሩ የአፍሪካ ፖለቲካ... በስማዳ ወረዳ የታሪካዊ ቦታ ጉብኝት ተደረገ በስማዳ ወረዳ የታሪካዊ ቦታ ጉብኝት ተደረገ በወረዳ ካሉ ታሪካዊ ገዳማት መካከል በቀበሌ 35 የደብረ እንቁ ማሪያም ገዳም አንዱ ሲሆን ከስወ/ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ጋር በመተባበር በክብር በአሉ በመገኘት ጉብኝት ተካሂዷል፡፡ የቀድሞ የገዳም አስተዳዳሪ የነበሩት መላከ ስብአት አረጋ ሠርፄ እንደገለጹት ገዳሟ በ33 ዓ/ም በካሌብ ዘመነ መንግስት የተተከለች መሆኗንና ለ20 አመትም በድንኳን የተቀመጠች እንደነበር ገልጸው በርካታ መነኩሳትም እንደሚኖሩባትና የድጓና የቅኔ መምህር በገዳሙ ያሉ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ገዳሙ ከየኳሳ ታዳጊ ከተማ በእግር መንገድ 1 ስዓት የሚወስድ ሲሆን ከተራራ ላይ የተሰራ ስለሆነ ወደ ገዳሙ የሚመጡ ተገልጋዩች መንገዱ ከአንድ ሰው በላይ የማያስተላልፍ ስለሆነ እየተጠባበቁ ወደ ገዳሙ ይዘልቃሉ፡፡ መ/ር መስፍን እዘዘው በበኩላቸው እንደገለጹት በገዳሙ ሲያገለግሉ የቆዩ አቡነ ፋሊጶስ 12 አመት ካገለገሉ በኋላ ሲያርፉ ከቤተክርስቲያኑ የቅዳሴ ቦታ ላይ መቀበራቸውን ፣ ለምፅ እያነፁና ጐባጣ እያቀኑ የኖሩ አባት እንደሆኑ ገልጸው በገዳሙ የቀብር ስርዓት ሲኖር አስከሬኑ በሁለት ሰው ብቻ ተይዞ የሚሄድ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ገዳሙ ከፍተኛ ተራራ ላይ የሚገኝ ሲሆን ተራራው የመስቀለኛ ቅርጽ ያለውና ገዳሟ እስከ 1958 ድረስ ስር የለበሰች እንደነበረችና ከዚህ በላይ ቆርቆሮ እንደለበሰች ይነገራል፡፡ በገዳሙ ዙሪያ ያሉ ዝንጀሮዎች የቤተ ክርስቲያኑን ግብር እያዩ የማይባሉት መሆኑንና በድሮው ጊዜ ገዳማ ደብረ ሃቃይ እንደምትባልና አንድ ንጉስ ከገዳሙ ላይ ወርቅ ይታያል በማለት ደብረ እንቁ እንዳላት ይነገራል፡፡ በመጨረሻም የስወ/ቤተ ክርስቲያን ስራ አስኪያጅ የሆኑት ቄስ በውቀት መንገሻ እንደገለጹት ከስወ/ባህልና ቱሪዝም ጋር በመተባበር ይህንን ታሪካዊ ገዳም መጐብኘት መቻላችን ጥሩ መሆኑን ገልጸው በገዳሙ ያሉ አንዳንድ ችግሮችን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ማስተካከል እንዳለብን አይተናል ብለዋል፡፡ |
|
Design by endris essa second year database student